Child Care and Protection Child Care and Protection

Child Care and Protection
  • Information
  • Gallery
  • Related Contents
የሲዳማ ልማት ማህበር በሀዋሳ ከተማ ቱላ ክ/ከተማ ጨፌ ኮቲ ጃቤሳ የመ/ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም አስጀመረ በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሽት መንገሻ በንግግራቸው ይህ ትምህርት ቤት ተጨማሪ እና አራተኛ መሆኑን ገልፀው ቀደም ሲል በዚሁ በቱላ ክ/ከትማ ሦስት ትምህርት ቤቶች ያስጀመርነው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በዚህ ጊዜም ተጠናክሮ ከመቀጠሉም...

What's included

የሲዳማ ልማት ማህበር በሀዋሳ ከተማ ቱላ ክ/ከተማ ጨፌ ኮቲ ጃቤሳ የመ/ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም አስጀመረ

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሽት መንገሻ በንግግራቸው ይህ ትምህርት ቤት ተጨማሪ እና አራተኛ መሆኑን ገልፀው ቀደም ሲል በዚሁ በቱላ ክ/ከትማ ሦስት ትምህርት ቤቶች ያስጀመርነው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በዚህ ጊዜም ተጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ ጥሩ ልምድ ያገኘንበት ነው ብለው ተማሪዎችን በአግባቡ ከያዝናቹው የሀገር ሀብቶች መሆናቸውን ተረድተን ሁላችንም ይህን አላማ ልደግፍ ይገባል ብለዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የአከባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት ልማት ማህበሩ የጀመረውን ይህን መልካም ተግባር ከጎኑ በመቆም ልንደግፍ ይገባል ካሉ በኋላ የሲዳማ ልማት ማህበር በሦስት ት/ቤቶች ያስጀመረውን የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ቀጥሎ የዚህ ትምህርት ቤት ተማሪዎችንም ተጠቃሚ በማድረጉ ደስተኞች እንደሆኑና ምገባው ባልተዳረሰባቸው ትምህርት ቤቶች እንዲዳረስ የሁላችንም ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

Partners
Our Newsletter

Subscribe to our newsletter and get exclusive first-minute news straight into your inbox.


    Our Newsletter

    Subscribe to our newsletter and get exclusive first-minute news straight into your inbox.


      https://sida.org.et/wp-content/uploads/2024/09/cropped-Logo-Full-Color-10.png

      Visit us on Social Networks

      https://sida.org.et/wp-content/uploads/2025/05/qrcode_211100729_84b73c1cbf13becb83c95b7bdd8d7be7-160x160.png
      All Rights Reserved. © 2025
      Sidama Development Association

      Powered By Sumuda Technologies – Hawassa

      Visit us on Social Networks

      All Rights Reserved. © 2025
      Sidama Development Association

      Sumuda Technologies – Hawassa