Child Care and Protection
Child Care and Protection
- Information
- Gallery
- Related Contents
What's included
የሲዳማ ልማት ማህበር በሀዋሳ ከተማ ቱላ ክ/ከተማ ጨፌ ኮቲ ጃቤሳ የመ/ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም አስጀመረ
በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ወይንሽት መንገሻ በንግግራቸው ይህ ትምህርት ቤት ተጨማሪ እና አራተኛ መሆኑን ገልፀው ቀደም ሲል በዚሁ በቱላ ክ/ከትማ ሦስት ትምህርት ቤቶች ያስጀመርነው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በዚህ ጊዜም ተጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ ጥሩ ልምድ ያገኘንበት ነው ብለው ተማሪዎችን በአግባቡ ከያዝናቹው የሀገር ሀብቶች መሆናቸውን ተረድተን ሁላችንም ይህን አላማ ልደግፍ ይገባል ብለዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የአከባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት ልማት ማህበሩ የጀመረውን ይህን መልካም ተግባር ከጎኑ በመቆም ልንደግፍ ይገባል ካሉ በኋላ የሲዳማ ልማት ማህበር በሦስት ት/ቤቶች ያስጀመረውን የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ቀጥሎ የዚህ ትምህርት ቤት ተማሪዎችንም ተጠቃሚ በማድረጉ ደስተኞች እንደሆኑና ምገባው ባልተዳረሰባቸው ትምህርት ቤቶች እንዲዳረስ የሁላችንም ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።


