የሲዳማ ልማት ማህበር ዛሬ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አዲስ ቦርድ አባላትን ጨምሮ የተለያዩ መተዳደሪያ ደንቦችን አጽድቀዋል። የሲዳማ ልማት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ ቦርድ ሰብሳብ እና አባላትን ሰይሟል በዚሁ መሠረት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ዶ/ር አያኖ ባራሶ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ሐገረፅዮን አበበ እና አምስት አባላትን የመረጡ ሲሆን በዚህ መሰረት:- 1.ቄስ ኢያሱ ጣጊቾ 2.አቶ ተሰማ ሕርባዬ 3. ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ 4.አቶ ብሩ ወልደ 5.አቶ ማቶ ማሩን የቦርድ አባላት እንዲሆኑ ጠቅላላ ጉባኤው ወስኗል። በሌላ በኩል አዲስ የተቋቋመው ቦርድ ወ/ሮ ወይንሸት መንገሻን የሲዳማ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ የመረጠ ሲሆን የአዲሱ የመስሪያ ቤቱ ሎጎ እና ለሪፎርም የሚያግዙ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ውይይት በማድረግ በጉባኤው ፀድቋል።




