“የሲዳማ ልማት ማህበርን በእውቀት እና በስትራቴጂ በመምራት የበለፀገ የሲዳማ ማህበረሰብን ለመፍጠር ይሰራል።” ርዕሰ መስተዳድር አቶ አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ልማት ማህበርን በእውቀት እና በስትራቴጂ በመምራት የበለፀገ የሲዳማ ማህበረሰብን ለመፍጠር ይሰራል ሲሉ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ። “ለሲዳማ እድገት የድርሻዬን እወጣለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ የተቋሙን ሪፎርም በተመለከተ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኘበት የሲዳማ ልማት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። በዕለቱ ጉባኤውን በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የህዝብ ሀብትን በአግባቡ በመምራት የበለፀገ የሲዳማ ማህበረሰብ መፍጠር ይቻላል በማለት ይህን ለማድረግ ያለንን እምቅ አቅም በመጠቀም ቀጣይነት ያለውን ለውጥ ለማስመዝገብ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። በተጨማሪም የሲዳማ ልማት ማህበር ባለፉት 30 አመታት በ30 የገጠር ወረዳዎች እና በ6 ከተማ መስተዳድሮች በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ሲሰራ የቆየ ተቋም ነው በመሆኑም አሁን የበለጠ ተደራሽ እንዲሆንና ጠንካራ የልማት ተቆርቋሪ ለማድረግ የተጀመረው ሪፎርም ተግባራዊ እንዲሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ይጠይቃል በማለት ተናግረዋል። የሲዳማ ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወይንሸት መንገሻ እንደተናገሩት ማህበሩ በ1985ዓ.ም ከተመሠረተ ጀምሮ የህብረተሰቡ የመልማት ፍላጐት ለሟሟላት የድርሻውን ሲወጣ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ባለፉት 30 አመታት ብዙ ስራ መስራት ቢቻልም የታቀደውን ያህል ውጤት ማስመዝገብ አልተቻለም ብለው ይህን ለመቅረፍ ተቋሙን ሪፎርም የማድረግ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።






2 comments
Alemseged Matusala
April 8, 2024 at 7:57 am
Good Progress. Keep it up.
WebAdmin
April 8, 2024 at 7:59 am
Thank you for your kind comment!